aatvetagency.gov.et: Cutting your costs, fighting your corner

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ

English

 

ኤጀንሲው ለቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች ሥልጠና እየሰጠ ነዉ

 

06-ሐምሌ-2012

ከኤጀንሲ ኮሙኒኬሽን

የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሚሠሩ አሠልጣኞች ከህሎት መዳበር እንዳለበት ተጠቆመ፡፡ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኤጀንሲ ከ1200 በላይ ለሚሆኑ አሰልጣኞች የክህሎት ማሻሻ ያ የክረምት መርሃ ግብር ስልጠና እየሠጠ ነው፡፡

ከሠልጣኞቹ መካከል 506 ያህሉ በ11 የተለያዩ የሙያ ዘርፎች በኢንዱስትሪዎች የሚሠለጥኑ ሲሆን፤ ቀሪዎች 589 ሠልጣኞች ደግሞ በኤጀንሲው ሥር ባሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጆችና ተቋማት በ17 የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ነው እየሠለጠኑ ያሉት፡፡

በስልጠናው የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾችን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት፣ የጥራት ሥራ አመራር ወይም ካይዘን እንዲተገብሩ ብሎም ምርታማነታቸው እንዲጨምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርንና የስራ ፈጠራ ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰጠ እንደሆነ አቶ ሲሳይ አስታውቀዋል፡፡

ስልጠናው አብዛኛዎቹ ሙያዎች በመንግስት ኮሌጆች ግብአት እየተማሉ ከፊሊፕንስ በመጡ አሰልጣኞች መሪነትና ከመምህራኖችም የተሸለ ዕውቀትና ክህሎት ያላቸው በእረዳት አሰልጣኝነት እየሰሩ እንደሚማሩ የስራሂደት መሪው ገልፀዋል፡፡ የዘንድሮው የክረምት መርሃግብር ስልጠና አራቱም የኢንዱስትሪ ፓኬጆች መሰረት ያደረገ ፕሮጀክት ተቀርፆ መዘጋጀቱ ከባለፈው አመት የተለየ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

በሌሎች 6 የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለ131 ሰልጣኞች የክህሎት ማሻሻያ ስልጠናውን ለመስጠት የታቀደ ቢሆንም በማሰልጠኛ ቦታ እጥረት ምክንያት አለመሰጠቱ ከጋዜጣዊ መግለጫው ለማወቅ ተችሏል፡፡